የሉሲ ቅሪተ አካል ለተገኘበት የአፋር ክልል አደአር ወረዳ መሰረተ ልማት ግንባታና የልማት አውታር ዝርጋታ የተመደበው የ6.7 ሚሊዮን ብር በጀት ተጠያቂነት በሌለው የክልሉ የፋይናንስ አሰራር መሰረት ለአደአር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ገቢ ሊደረግ መሆኑ ታወቀ።
ሉሲን ጨምሮ አርዲ፣ ከዳባ፣ ሰላም… የመሳሰሉ በርካታ ዝነኛ እድሜ ጠገብ ቅሪቶች የተገኙበት አደአር ለሳይንሱ አለምና ለሀገራችን መልካም ገጽታ ግንባታ ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከት ቢችልም በአካባቢው መሰረተ ልማት አለመዘርጋቱ ለዘርፉ ተመራማሪዎችና ቱሪስቶች እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል።
በቅርቡ ኢዜአ የጥናት ቅርስ ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው ከአውሮፖ ህብረት በተገኘ 400 ሺህ ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ስፍራውን የማልማት ቅደመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ነው። እንደዘገባው በመስኩ ሊገንቡ የታሰበው ለተመራማሪዎችና ጎብኚዎች መረጃ የሚሰጥ ማዕከልና የሙዝየም ግንባታ እንደሚከናወን ጠቁሞ በተጨማሪም እስከ 40 የሚሆኑ የአካባቢውን ወጣቶች በእደ-ጥበብ ሙያ በማሰልጠን ወደስራ የሚገቡበት የመንቀሳቀሻ ገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው አስታውቀዋል።
ይሁን እንጂ ስሙን ያልጠቀስነው ግለሰብ የላከልን የምስል ማስረጃ እንደሚያመለክተው የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የጥናትና ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን አካባቢውን ከጎበኘና ከወረዳው ባለስልጣናት ጋር በአካል ተገናኝቶ ከተወያየ በኋላ የክልሉን የፋይናንስ አሰራር መሰረት በማድረግ በጀቱን ለወረዳው ባለብዙ ስልጣን (የወረዳው ወ/አስተዳደር፤ ዋና ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ፤ ውኃ ሃብት ጽ/ቤት ሃላፊ፤ ንግድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ…) በሆኑት አቶ መሀመድ ሳኒ አሊ የሚንቀስ የባንክ አካአካውንት ለመላክ መወሰኑን ታውቋል።
ይህ አሰራር በአፋር ክልል ህዝብ ላይ የተከፈተ ስልታዊ የኢኮኖሚ ጦርነት ሲሆን አፋር ለ27 አመታት በህግ ሽፋን ሲበዘበዝ የኖረበት አሰራር መሆኑን በክልሉ ህዝብ ዘንድ ስፋት ይታወቃል። የተፈጥሮ ሀብት ባለቤቱን የአፋርን ህዝብ ድህነት መጥቀስ በቂ ነው። በአፋር ክልል ያሉ ለቁጥር የሚያታክቱ አለማቀፍ የቱሪዝም መዳረሻዎች ከአፋር ህዝብ ይልቅ የፈየዱት ለፌደራልና ትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም መሆኑ ይታወቃል።
አገር በለውጥ ጎዳና ላይ መጓዝ በጀመረችበት በዚህ የተሃድሶ ወቅት የኢፌድሪ የጥናትና ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የመካነ-ቅርስ አስተዳደርና ልማት ዳይሬክተር ወይዘሮ ጸሐይ እሸቴ “የእከክልኝ ልከክልህ” ብልሹ የስራ ባህል ክልላዊ የፋይናንስ አሰራር በማስመሰል ያሳለፉት ውሳኔ በህግ ሽፋን ለግል ጥቅም ጥቅም የተሰጠ የህግ ሽፋን መሆኑ ግልጽ ነው። የኢዜአ ዜና እንደሚያመለክተው በእቅዳቸው መሰረት ወደ ዘረፋ ለመግባት የቀራቸው የ2 ወር ጊዜ ብቻ ነው። ይሁንና ወይዘሮዋ ከታህሳስ/2011 በፊት ሀሳባቸውን መቀየራቸውን እና ግንባታው ተጠያቂነትና ዋስትና ባለው ህጋዊ አሰራር መሰረት በክልሉ ውስጥ ላሉ ያየዘርፉ የግንባታ ተቋራጭ እና አማካሪ ድርጅቶች ጋር የስራ ውል ስምምነት በማደረግ የስራ ውል ስምምነት መሰረት ካልተከናወነ በጉዳዩ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው መረዳት ይኖርባቸዋል።
በክልሉ መንግስት የለውጥ አብዮትን ያፈነዱ የክልሉ ወጣቶች (ዱኮ-ሒና) ጉዳዩን በሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴያቸው ውስጥ የትግል ፕሮግራማቸው አካል በማድረግ እስከ መጨረሻው የፍትህ ደጅ እንደሚዘልቁ ተስፋ አለኝ።